የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
የውስጥ ደዌ ህክምና
- የሳንባ፣ የጉበት፣ የኩላሊት ምርመራና ህክምና መስጠት
- የጨጓራ፣ የእንቅርት ምርመራና ህክምና መስጠት
- የስኳር፣ የደም ግፊት ምርመራና ህክምና መስጠት
- የተለያዩ አጣዳፊ ህመሞች ምርመራና ህክምና
- አጠቃላይ ከፍተኛ የአዋቂዎች ምርመራና ህክምና መስጠት
የማህፀንና ፅንስ ህክምና
- የቅድመ ወሊድና የድህረ ወሊድ ክትትል
- የማዋለድ አገልግሎት
- የመካንነት ምርመራና ህክምና
- የኦፕራሲዮን አገልግሎት
- የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራና ህክምና
- የተለያዩ ከማህፀን ውጪ ምርመራና ኦፕራሲዮን
- የማህፀን ውልቃት /ፕሮላፕስ/ ምርመራና ኦፕራሲዮን
- የስነተዋልዶ ምጣኔ አገልግሎት
- የአባላዘር ህመም ምርመራና ህክምና
የህፃናት ህክምና
- የሳንባ፣ ኩላሊት፣ ስኳር ምርመራና ህክምና
- የህፃናት እድገት ክትትል
- ከደም ጋር የተያያዙ ህመሞች ምርመራና ህክምና
- አጣዳፊ የሆኑ የህፃናት ህመሞችን ምርመራና ህክምና
የቀዶ ጥገና ህክምና
- የትርፍ አንጀት ኦፕራሲዮን
- የሀሞትና የኩላሊት ጠጠር በቀዶ ህክምና
- የአንጀት መታጠፍ ኦፕራሲዮን
- የእንቅርት ኦፕራሲዮን
- የኪንታሮት ኦፕራሲዮን
- የተለያዩ የድንገተኛ ኦፕራሲዮን ሥራዎች
- የሄርኒያ ኦፕራሲዮን
- የዘር ፍሬ እብጠት ኦፕራሲዮን
- የወንድ ልጆች ግርዛትና የተለያዩ ቀላል ኦፕራሲዮኖች
የስነ ደዌ ህክምና
- በተለያየ የሰውነት ክፍል የሚወጡ እጢዎችና እባጮች ምርመራ
- የማህፀን በር ካንሰር /ፓፕስሚር/ ምርመራ
- የደም ካንሰር ምርመራ
- ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚወጡት ፈሳሾች መመርመር
የአይን ህክምና
- የአይን እይታ ችግሮችን ምርመራና ህክምና
- በኦፕራሲዮን የሚስተካከልን የአይን ችግር መኦፕራሲዮን ማከም
- የተለያዩ የአይን ችግሮችን መለያ ምርመራ ማድረግ
- የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና
የቆዳና የአባላዘር ህክምና
- በተለያየ ምክንያት ቆዳ ላይ የሚወጡ ችግሮችን በመድሃኒትና በኦፕራሲዮን ማከም
- የአባለዘር ህመም ማከም
- የተለያዩ ለቆዳ ህመም የሚሆኑትን መድሃኒቶች መቀመም
የአንጎል ህብለ- ሰረሰር (የነርቭ) ቀዶ-ህክምና
- የዲስክ መንሸራተት በኦፕራሲዮን ማስተካከል
- በህብለሰረሰር ችግር የሚመጡ የነርቭ ችግሮችን መመርመርና ማከም
የፊዚዮቴራፒ አገልግሎት
- በተለያየ ህመም ምክንያት የሚከሰት የሰውነት ያለመታዘዝ ህክምና
- በአደጋ ምክንያት የሚመጣን የአካል እንቅስቃሴ መቀነስ ህክምና
- በነርቭ ችግር የሚመጣን የሰውነት እንቅስቃሴ መቀነስ ህክምና